የእስልምና አክራሪንት አደጋ በኢትዮጵያ

burnt-church
የስልምና አክራሪነት ና ኢትዮጵያ
የመብት ጥያቄ በሚል ሽፋን  ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋና ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ  የመጣውና ብዙዎችን ግራ እያጋባ ያለው የሙስሊሞችን ጥያቄ መመርመርና ስር መሰረቱን ማጥናት አስፈላጊ ነው።ብዙዎች ጉዳዩ ከመብት ጥያቄ ጋር በማያያዝ ብቻ ጉዳዩን አቃሎ የማየት ችግር ይታያል። ይህንን ስህተት ማረም ግድ ስለሚል እኔም የማውቀውን  ለማካፈል ብእሬን አነሳሁ።
ብዙዎች እንደሚያስቡት ጉዳዩ አሁን የጀመረና የመጅሊስ ጉዳይ ጋር ተያይዞ የመጣ አይደለም ።  ኢትዮጵያ ውስጥ እስላማዊ መንግስትን የመፍጠርን አላማ አርጎ ሚንቀሳቀሰው ቡድን በጉዳዩ  ላይ ከ16 አመት በላይ በከፍተኛ ሁኔታ ሲሰራ ቆይትዋል።ይህንን ጉዳይ ለመንግስት ተደጋጋሚ ጥቆማዎች ቢደረጉም መንግስት ጉዳዩን ጆር ዳባ ልበስ በማለቱ ስር እንዲሰድና  ጉዳዩ አሁን የደርሰበት ደርጃ ላይ እንዲደርስ ሆንዋል። ሙስሊም በሌለባቸው ቦታዎች መስኪድ በመስራት እንደዚሁም ከቤተ ክርስቲያን አጠገብ መስኪድ የመስራት ፤ ክርስቲያኖችን የመግደልና ቤተክርስቲያንን የማቃጠል እርምጃዎች በተደራጀ መልኩ ሲሰራበት ቆይትዋል።
ጉዳዩ አደባባይ ያወጣው ግን  በ ሚያዚያ  ወር 2008 የተከሰት አንድ ክስተት ነበር። ጉዳዩም ይህ ነበር። አንድ ባህታዊ ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ውጭ ሆኖ ጸረ እስልምና የሆነ ንግግር ያደርግ ነበር። ይህንን አጋጣሚ ሲጠብቁ የነበሩ የእስልምና አክራሪዎች ወደያው በስልክ ካሜራ በመቅረጽ የድህረ ገጻቸው ላይ ያወጡታል።ወዲያውም ድህረገጾችንና በየፓልቶክ ሩሞቹን በመጠቀም  ከፍተኛ ጸረ  ኦርቶዶክስ  ዘመቻ ተጀመረ። ተደብቆ የነበረ ጥላቻ የወጣ ጀመር። ባህታዊው ግለሰብ ንግግሩን ያደረግ የነበረው ከቤተክርስቲያን ውጭ የነበረ በመሆኑና  ፣ንግግሩም እራሱን ወክሎ እንደሆነ እየታወቀ ።ይህንን አጋጣሚ እንደወርቃማ እድል ይጠብቁ የነበሩት አክራሪዎች ጉዳዩን ወደ ኢንተርኔት በማምጣት በከፍተኛ ሁኔታ አባባሱት ።ወዲያውም  እነአቶ ነጂብ የሚመራው ፈርስት ሂጅራ ድርጅት  ዲሲ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ። ጉዳዩን ከሚገባ በላይ በማጮህ ይህንን ባህታዊ  ይሰቀል ይሉ ገቡ ፡፡ ይህ ለመነሳት ጊዜ ይፈልግ የነበረው አክራረው ብድን  ኢንተርኔትን  በመጠቀም  ከፍተኛ የሆነ አንቲ ኦርቶዶክስ የሆነ ጣላቻ ያስፋፋ ጀመር ።  አክራሪው ብድን አንድ ታርጌት ያደረገው ቪኦኤን ሲሆን የቪኦኤው አዲሱ አበበን የቤተክርስቲያን ቀዳሽ ነበር።ቪኦኤ የኦርቶዶክስ ነው ብለው ይዘጋ ዘንድ ፒቴሽን ፈርመው ለቪኦኤ አስገቡ።
አገር ቤት ውስጥም  ከፍተኛ የማደራጀትና ኔትወርክ የመፍጠር ስራ ተጀመረ።በጋሞጎፋ በ ስልጤ አካባቢ የታየው ቤተክርስቲያንን የማቃጠል እርምጃ አንድ ማሳያው ነበር።በማስከተለም ገዳማትን ጫካ እሳት መለኮስ፤ በመስሊም አካባቢ ሚገኙ ክርስቲያኖችን የማስፈራራት ብሎም የመግደል እርጃ ይወሰድ ጀመር።
ሁኔታው በዚህ ላይ እያለ የመጅሊሱ ጉዳይ በማራገብ ሙስሊምን ለማነሳሳት ተጠቀሙበት፡ጉዳዩን የሂውማን ራይት ጉዳይ በማስመሰል ድብቅ አላማቸውን ለማስፈጸም ተግተው ሰሩ። የውጭ ሚድያዎችን ማለትም  አልጀዚራን የመሳሰሉትን  በመጠቀም ሙስሊሞች እየተበደሉ ነው በማለት በአረብ አገራት ሚኖሩትን ኢትዮጵያውያንን አደጋ ላይ በሚጥል መልኩ ተንቀሳቅሰዋል ።
ክርስቲያኑ ህዝብ ጉዳዩን ወያኔ ነው ብሎ በጭፍን  ጉዳዩን በቸልታ ባያልፉት መልካም ነው። አክራሪነት በአለም ላይ የተደቀነ አደጋ ነው። አክራሪዎቹ ጉዳዩን የሰብአዊ መብት ጉዳይ በማስመሰል የሚያረጉትን እንቅስቃሴ በጥልቀት ሊከታተለው ይገባል
ቸር ይግጠመን
ይማም በላይ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s